ESTABLISHED IN 06-05-2006 G.C

DORPSTRAAT 18, 5504 HH VELDHOVEN

About The Church

The Ethiopian Orthodox Tewahedo Church in Veldhoven was first established in 2006 in collaboration with members of the Ethiopian churches in Europe at Eindhoven, the Netherlands. In 2020, the Veldhoven Tsireha Aryam Holy Trinity Church was recognaized by Ethiopian Orthodox Tewahedo Church and an administrative was assigned by the German and EU Tewahdo church members diocese. In the same year, the church recieved its Tabot. The Church is currently providing full service to its congregation at a rented Church located at Dorpstraat 18, Veldhoven once in every two weeks.

በቬልዶቨን የምትገኘው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን በሰንበት ት/ቤት ደረጃ በአውሮፓ አቆጣጠር (እ.ኤ.አ.) በ 06/05/2006 ተመሰረተች። በአውሮፓ አቆጣጠር (እ.ኤ.አ.) በ 25/01/2020 በ ቤ/ክ ደረጃ የተሰየመች ሲሆን ፣ እንዲሁም ከጀርመንና አካባቢው ሀገረ ሰብከት አስተዳዳሪ ተመደበላት። በዚያው ዓመት የቬልድሆቨን ፀረሀ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን እውቅና አግኝታ ከብፁህ አብነ ዲዮናስዮስ ተድላ የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ሰብከት ጳጳስ ጽላት ተቀበለች። ቤተክርስቲያኗ በአስራ አምስት ቀን አንድ ጊዜ በዶርፕስትራአት 18 ቬልድሆቨን በተከራየችው ቤተክርስቲያን ለምእመናኗ ሙሉ አገልግሎት እየሰጠች ትገኛለች።

Vision

- To enable religious followers aware of their spiritual assets, values, traditions and able them to keep it up.
- To strengthen the overall spiritual as well as social status of the church.
- To teach the religious followers and enable to receive spiritual service in the required way under the doctrine of the church.
- To expand worshiping as well as disciplinary activities of the church.

- የሀይማኖት ተከታዮች መንፈሳዊ ህይወታቸውን ፣ እሴቶቻቸውን እንዲሁም ባህሎቻቸውን እንዲያውቁ እና እንዲቀጥሉ ማድረግ።
- የቤተ ክርስቲያኗን አጠቃላይ መንፈሳዊ እና ማህበራዊ ደረጃ ለማጠናከር።
- የኦርቶዶክስ ሃይማኖት ተከታዮችን በማስተማር በቤተ ክርስቲያኗ አስተምህሮ በሚፈለገው መንገድ መንፈሳዊ አገልግሎት እንዲያገኙ ማስቻል።
- የቤተክርስቲያንን አምልኮ እና የዲሲፕሊን ተግባራትን ማስፋፋት።

Mission

- To enable the church to play its role in the social and historical formation of the othodox tewahdo church.
- To facilitate a situation that the religious followers of the church could be able to serve the church
   through their knowledge and labor.

- ለኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ማኅበራዊና ታሪካዊ ምስረታ ቤተ ክርስቲያን የበኩሏን ሚና እንድትወጣ ለማስቻል።
- የቤተ ክርስቲያኗ የሃይማኖት ተከታዮች ቤተ ክርስቲያኗን በእውቀታቸው እንዲሁም በጉልበታቸውየሚያገለግሉበትን ሁኔታ ለማመቻቸት።
- በኔዘርላንድ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያን-የአይንድሆቨን ጽርሐ አርያም ቅድስት ሥላሴ ቤተ ክርስቲያን ከመናፍቃንና
  ከተሐድሶ በጸዳ መልኩ አንድነቷን በመጠበቅ የተሟላ የካሕናት አገልግሎት እንድታገኝ ለማድረግ።
- ከአገራቸው በስደትና በሌላ ምክንያት ወጥተው ቤኔዘርላንድና አካባቢው የሚኖሩ ምዕመናንን በማሰባሰብ፤ በመንፈሳዊ ዕውቀት ጎልምሰው፣
  በምግባርና በሃይማኖት ጸንተው በክርስቲያናዊ ሕይወት እንዲኖሩ አስተዋጽኦ ለማድረግ።
- ቤተ ክርስቲያኒቱን-በኔዘርላንድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተክርስቲያንና ከቃለ አዋዲው ጋር በተገናዘበ መልኩ በመምራትና በማሳደግ   እራሷን እንድትችል ማድረግ።

OUR PRIESTS

Kesis Abraham Tsegaye

ቀሲስ አብርሃም ፀጋዬ